የቋንቋ ተደራሽነት እና ጥራት ያለው እንክብካቤ የማግኘት መብትዎ
እያንዳንዱ ታካሚ የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶችን በሚገባው ቋንቋ የማግኘት መብት አለው። ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ስጋቶችን መግለጽ እና ከዶክተሮችዎ እና ከጤና እንክብካቤ ቡድንዎ ጋር ውጤታማ በሆነ መንገድ መግባባት መቻልዎ በጣም አስፈላጊ ነው። ለዚያም ነው M Health Fairview በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት ሰባት ቀን ነጻ የአስተርጓሚና የጽሑፍ ትርጉም አገልግሎትን እንዲሁም የተግባቦት (የኮሙዩኒኬሽን) መርጃዎችን የሚያቀርበው። በሚከተሉት ሁኔታዎች ወቅት አስተርጓሚ መጠየቅ ይችላሉ፦
- ቀጠሮዎን ሲይዙ
- ከቀጠሮዎ በፊት በማንኛውም ጊዜ
- ለቀጠሮዎ ሲደርሱ
- በቀጠሮዎ ወቅት በማንኛውም ጊዜ ለሰራተኛ አባል የአስተርጓሚ አገልግሎት እንደሚፈልጉ ሲነግሩ።
እንዴት ነው የሚሰራው?
የአስተርጓሚ አገልግሎቶች በቀን 24 ሰዓት፣ በሳምንት ሰባት ቀን በነፃ ይገኛሉ። በአካል፣ በስልክ እና በቪዲዮ አስተርጓሚዎች በብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ። የስልክ እና የቪዲዮ አስተርጓሚ አገልግሎቶች ወደ 250 ገደማ ቋንቋዎች እና የአነጋገር ዘዬዎች በተፈለጉ ወቅት ይገኛሉ።
ለሚከተሉት ቋንቋዎች በአካል የአስተርጓሚ አገልግሎቶች ይገኛሉ፡-
- ስፓኒሽ
- ሶማሊኛ
- ሃሞንግ/ላኦ
- ኦሮምኛ/አማርኛ
- ካረን
- ASL
- ራሽያኛ
- ቬትናምኛ
- ካምቦዲያኛ
- ሌሎች በጥያቄዎ መሰረት
እንዲሁም ተጨማሪ የተግባቦት (ኮሚዩኒኬሽን) መርጃዎችን፣ በአስተርጓሚና በኮምፕዩተር የታገዘ ንግግርን ውዲያውኑ ወደ ጽሑፍ የመቀየር (ካፕሽኒንግ) አገልግሎት፣ እና ለታካሚ የትምህርት ቁሳቁሶች የጽሑፍ ትርጉም አገልግሎቶችን እናቀርባለን።
የመጀመሪያ ጉብኝትዎን በምናቅድበት ጊዜ ስለ ተመራጭ ቋንቋዎ እና የአስተርጓሚ አገልግሎት ይፈልጉ እንደሆነ እንጠይቃለን። አንዴ የአስተርጓሚ ፈላጎቶችዎ በቻርትዎ ውስጥ ከሆኑ፣ በእያንዳንዱ ጉብኝት ላይ የአስተርጓሚ አገልግሎቶችን እናዘጋጃለን።
መስማት የተሳናቸው እና የመስማት ችግር ያለባቸው አገልግሎቶች
መስማት ለተሳናቸው፣ መስማት እና ማየት ለተሳናቸው፣ ወይም የመስማት ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የምስክር ወረቀት ያላቸው የ ASL (የምልክት ቋንቋ) አስተርጓሚዎችን ወይም CART (ንግግርን ውዲያውኑ ወደ ጽሑፍ የመቀየር አገልግሎት ሰጪዎችን) እናቀርባለን። የተግባቦት (ኮሚዩኒኬሽን) እርዳታ በጠየቁ ጊዜ በነፃ ይገኛሉ። እነዚህን አገልግሎቶች ከፈልጉ፣ እባክዎን ለማንኛውም ለ M Health Fairview ሰራተኛ ይንገሩ እና ምርጫዎችዎን ይግለጹ።
በቋንቋዎ የሚገኙ ሰነዶች እና ፖሊሲዎች
ሰነዶችን በመረጡት ቋንቋ ተርጉመናቸው ሊሆን ይችላል። እባክዎን ከታች ያግኙዋቸው።